ለሰብል ልማት ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው ውሃ፡፡ለልማቱ የሚውለው ውሀ በተፈለገው መጠን እና ወቅት መገኘት ይኖርበታል፡፡ለሰብል ልማት የሚውል ውሃ አንደኛው ከዝናብ የሚገኝ ሲሆን ሌላው በመስኖ ነው፡፡ ለመስኖ የሚውል ውሃ መገኛው የተለያየ ነው፡፡ የተለመደውና ረጅም ዘመናት ሲሰራበት የኖረው የወንዝ ውሀ ለመስኖ ማዋል ነው፡፡

 ግብፃውያን በአባይ ውሀ በመስኖ ሰብል አልምተው በማምረት በዓለም የረጅም ዘመን ታሪክ ባለቤት ናቸው፡፡ የአባይን ውሀ በካናል በመውሰድ ለልማት ማዋል ከጅመሩ ከስድስት ሽ አመታት በላይ ማስቆጠሩን የተለያዩ የታሪክ መዛግብት ይመሰክሩላቸዋል፡፡

በሌላ በኩል የአባይ ባለቤት፣የአባይ መገኛ የሆነችው ኢትዮጲያ በመስኖ የማልማት ተሞክሮዋ አንድ መቶ አመት አይሞላውም፡፡ግብፆች በመስኖ በሚያለሙበት ጥንታዊው ዘመን ኢትዮጲያውያን በመስኖ መጠቀም የግድ የሚላቸው አልነበረም፡፡ በተፈጥሮ በሚገኘው ዝናብ የሚፈልጉትን ሰብል ለማምረት ችግር አልነበረባቸውም፡፡

ሕዝብ እየጨመረ ሲሄድ ለምግብነት የሚውል ሰብል ፍላጎት መጠን አብሮ ይጨምራል፡፡ ከዝናብ ከሚገኝ ውሀ የሚለማው መሬት ግን መጠኑ ስለማይጨምር የምግብ እጥረት ይከሰታል፡፡ በሌላ በኩል የአየር ንብረት መዛባት ምክንያት የሚጥለው ዝናብ ወቅት መዛባት ፣መቆራረጥ፣መብዛትና ጭራሹንም ለተከታታይ አመታት ዝናብ ሳይጥል የሚቀርባቸው አመታት ኢትዮጵያውያንን ድርቅ በማስከተልና በድርቅ ተደጋጋሚ ክስተት በርሃብ ለእልቂት ሲዳርጋቸው ኑሯል፡፡

በድርቅና የአየር መዛባት በሰብል ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ወይም ኪሳራ ለመታደግ ግብርናው ከተፈጥሮ ዝናብ ጥገኝነት ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡ በ1994 ዓ.ም የተቀረፀው የኢትዮጵያ የግብርና ገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ በሰነዱ ያስቀመጠውን የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ግብ ለማሳካት ከተፈጥሮ ዝናብ ጥገኝነት ግብርናውን ለማላቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ ይገለፃል፡፡

በፖሊሲው ሀያ አመታት እድሜ ከዝናብ ጥገኝነት ለማውጣት በተለይ በአማራ ክልል የመሰኖ ልማት ተቋም አልተገነባምባይባልም  ክልሉ ካለው የከርሰ ምድር፤ የገፀ ምድር የውሀ ሀብት አኳያ መገንባት መልማት ከሚገባው መጠን አንፃር ሲታይ እጅግ በጣም አናሳ ነው ማለት ይቻላል፡፡

 

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

tototogel tototogel togel online