በአማራ ክልል በመስኖ ገብ መሬት የሚለማው የሰብል ምርት አልነበረም፡፡ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የግብርና ቢሮ በመስኖ ሰብል ማምረትን አይመክርም-አያስተምርም፡፡ በአማራ ክልል በበጋ በመስኖ የሚለማው አትክልት ብቻ ነው የነበረው ፡፡በቢሮው የተደራጀው ክፍል “የመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዳይሬክቶሬት “ ነው ስያሜው፤ ወደ ታች ሲወርድም በዚሁ ስያሜ የተደራጀ ነው፣ባለሙያዎቹ የዚሁ ዘርፍ ናቸው፣ኤክስቴንሽኑም በዚሁ እሳቤ የተቃኘ ነው፡፡

አትክልት ማልማት አስፈላጊ ነው ጠቃሚ ነው ፣ፍራፍሬ ማልማት አስፈላጊ ነው ጠቃሚ ነው፡፡  ነገር ግን በመስኖ ሰብል ማምረትን አለማካተቱ” በአመት ሶስት ጊዜ በማምረት ….. “የሚለውን የሚንድና የሚያመክን ነው የነበረው ልምድ፡፡

በመስኖ አትክልት በማልማት ከፍተኛ  ተጠቃሚ ለመሆን ከፍተኛ እንክብካቤ እና ግብዓቶችን መጠቀም ይጠይቃል፡፡ በቂ ውሃ ማግኘት መቻልም ይኖርበታል፡፡በዚህ ረገድ የሚሰጠው ኤክስቴሽን በርካታ አርሶ አደሮችን  መቅረፅ ችሏል ማለት ይቻላል፣ተጠቃሚ አድርጓል ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ በመስኖ በአትክልት ልማት ከፍተኛ ተጠቃሚ ሆኖ መዝለቅ ግን የሚያስችል አልሆነም፡፡ በክልሉ በሚገነቡ የመስኖ ተቋማት የሚካሄደው ልማት አትክልት ማምረት ላይ ብቻ ያተኮረ በመሆኑ የአትክልት አቅርቦቱ የአካባቢው ህብረተሰብ፣ከአካባቢው ራቅ ያሉ ከተማዎች ነዋሪ ከሚጠቀመው በላይ እየተመረተ የምርት መትረፍረፍ በተደጋጋሚ ተፈጥሯል፣አርሶ አደሩ ኪሳራ ላይ ወድቋል፡፡በ2013 ዓ/ም ቀይ ሽንኩርት ለማምረት ያወጡትን መጪ እንኳን የሚተካ ዋጋ ሳያገኙ ብዙዎች ከስረው ቀርቷል፡፡”ችግሩ የማነው?” ለሚለው ጥያቄ በመስኖ የሚካሄድ ልማትን ‹ በመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ዳይሬክቶሬት › እንዲመራና ‹ የሰብል ልማት ዳይሬክቶሬት ስራን በክረምት /በበልግ ዝናብ የሚካሄድ የሰብል ልማት ጉዳይ ላይ ብቻ እንዲሰራ ያደረገው አደረጃጀት የፈጠረው ችግር ነው ማለት ይቻላል፡፡

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

tototogel tototogel togel online