መሆኑን እንደ ችግር እየተጠቀሰም መሬቱን በመጠቀም በኩልም በአትክልት ልማት የታጠረውን መሬትም በሙሉ በመልማት አቅሙ መጠን ማልማትና  መጠቀም አለመቻልም ሌላው ችግር ነው፡፡ መስኖ ገብ መሬት በክረምት አንድ ጊዜ ይለማበታል፣በበጋ ደግሞ በመስኖ አንድ ጊዜ ይለማበታል፡፡ በበጋ በመስኖ ሁለት ጊዜ የሚለማበት መሬት መጠን እጅግ በጣም አነስተኛ ነው የነበረው ፡፡ በበጋ በመስኖ ሁለት ጊዜ ሊለማበት እየተቻለ ሳይሰራበት መቅረቱ እንደ አገር እንደ ክልል ኪሳራ ነው፡፡

በዚህ ሁሉ ችግሮች መሀከል ነው ‹ የበጋ የመስኖ የስንዴ ልማት” የመጣው ፡፡ የበጋ የመስኖ የስንዴ ልማትምን ይዞ ነው የመጣው? ፡

የበጋ የመስኖ ስንዴ የፖለቲካ ሰብል ነው በማለት ብዙዎች ይገልፀታል፡፡ የበጋ የመስኖ ስንዴ የፖለቲካ  ወይስ የኢኮኖሚ ሰብል ነው፡፡ፖለቲካን- ከኢኮኖሚ፤ ኢኮኖሚ ከፖለቲካ ነጥሎ ማየት ያስቸግራል፡፡ለማንኛውም መንግስት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ትኩረት ሰጥቶ በቅርቡ እየተከታተለ እየደገፈ ልማቱ እንዲካሄድ ያደረገበት ምክንያት አለው፡፡

ኢኮኖሚዋ በግብርና ውጤቶች ላይ የተመሰረተው የገበሬዎች አገር የሆነችው ኢትዮጵያ የግብርና አሰራሯን ወደ ዘመናዊነት በማሸጋገር ምርታማነቷን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የህዝቧን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የመንግስት ቀዳሚው ግብ ነው፡፡የግብርና ምርቶቿ በሌላው አለም ፣በጥራት ተመራጭ በዋጋ  ተወዳዳሪ ምርቶችን ወደ ውጭ  በመላክ የኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት ሀብት አንዲያስገኝ ይጠበቅበታል ግብርናው ፡፡በግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነድ እነዚህ ግቦች ለማሳካት መንግስት የግብርናው ዘርፍ ለማዘመን እንደሚሰራ ይጠቅሳል፡፡

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

tototogel tototogel togel online